ጣይቱ ታደሰ ትባላለች ተወልዳ ካደገችበት ምዕራብ ሸዋ በጊዜው በነበረ ድርቅ ምክንት ከአራተኛ ክፍል በኋላ ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ አዲስ አበባ መምጣቷን ትናገራለች፡፡ በነ ጣይቱ ቤት ህይወት ቀላል አልነበረም፡፡ ቤተሰቡ በጣም ዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝና ከእለት ጉርስ ያለፈ ጠብ የሚል ነገር አልነበረውም፡፡
ይህን ህይወት ታግላ የምታስታስተዳድረው ቤተሰቧን ችግር ለመቅረፍ አልቻለችም፡፡ ትምህርቷን እስከ አስራሁለተኛ ክፍል ብትገፋም ስራ ማግኘት ባለመቻሏ የቤተሰቧን ቀጣይ ሕይወት ያሻሽልልኛል ያለችውን ውሳኔ ወሰነች፡፡ ”ሴት ልጅ ስትሰደድ ለራሷ አይደለም ለቤተሰብ ወይ ለልጇ ብላ ነው“ የምትለው ጣይቱ በልጅነት የወለደችው ልጇን ለማስተማርና ታማሚ እናቷን ለመርዳት ስትል ወደ አረብ ሀገር ለመጓዝ መወሰኗን ትገልጻለች፡፡

ጣይቱ በ1995 ዓ.ም ህጋዊ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት መንገድን በመከተል ጉዞዋን ወደ ሊባኖስ አደረገች፡፡ የመጓዟ አንደኛው ምክንያት የሆኑ ታማሚ እናቷን በቅርበት ሳታስታምም፤ እንዳሰበችውም ለማገዝ ሳትበ በሄደች በሦሥት ወሯ እናቷን አጣች፡፡ ልጇን አስተምራ ለቁምነገር የማብቃት ህልሟን ሰንቃ የሊባኖስ የስራ ቆይታዋን ቀጠለች፡፡
ህጋዊ መንገድን በመከተሏ፤ በስራዋ ዙሪያ ስልጠና አግኝታና የስራ ሁኔታዋን አውቃ በመሄዷ በአግባቡ ደሞዝ ማግኘት መቻሏን ትናገራለች፡፡ ከዚህም ባለፈ ችግር ቢያጋጥማት በሊባኖስ ካለው ቆንፅላ ጽ/ቤት እና ከኤጀንሲ ጋር በመገናኘት መፍታት የምትችልበትን እድል ህጋዊነቷ የሚሰጣት መሆኑን ትናገራለች፡፡ በሊባኖስ የመጀመሪያ ዙር ጉዞዋ አምስት አመት የቆየች ሲሆን የሁለት አመት ኮንትራቷ ሲልቅ ከአሰሪዎቿ ጋር ግንኙነቷ መልካም የሚባል ስለሆነ በፍቃደኝነት ኮንትራቷን አድሳ ቀጥላለች፡፡ ”ህጋዊ መሆኔ ቢታወቅም ለአምስት አመት እዛ ቤት ስሰራ የረፍት ቀኔ ተሰጥቶኝ ወደ ውጭ ወጥቼ አላውቅም“ የምትለው ጣይቱ አሰሪዎቿ የተለያዩ ቤተሰቦቻቸው ጋር እያዘዋወሩ ያሰሯት እንደነበር ትገልፃች፡፡

የተሰጣት የኤጀንሲና የቆንፅላ ፅፈትቤቱ ስልክ በመጥፋቱ፣ በሰኣቱ ስልክ ስላልነበራት፣ ያለነሱ ፈቃድ መደወልም ስለማትችል እና ከዚህ ባለፈ አስተዳደጓ በይሉኝታ እድትታጠር አስተዋፆ ስለነበረው ይህ ሁሉ ተደማምሮ መብቷን እንኳ መጠየቅና ማስከበር ሳትችል መቅረቷን ትናገራለች፡፡ ደሞዝ በአግባቡ ቢከፈላትም ለአምስት አመት ከቤት ሳትወጣ በመቆየቷ “ፀሐይ እንኳን ይናፍቃል” ትላለች፡፡
ውጤት ባይመጣላትም በትምህርት ጥሩ ስለነበረች፤ በትምህርት የመዝለቅ ዓላማ ነበራት፡፡ እሷ ያጣችውን ልጇም እንዳያጣ ስለጉብዝናው መስክራ የማትጠግበው ልጇን ጥሩ ደረጃ ለማድረስ እያሰበች ትሰራ ነበር፡፡ ልጇን ዘመድ ቤት አስቀምጣው ስትሄድ በነበረው ቆይታ ብዙ እንግልት ደርሶበታል፡፡ ዘመድ ጋር መቆየት ምቹ አልነበረም፡፡ በ2000 ዓ.ም ልጇ ስምንተኛ ክፍል ሲደርስ ተመልሳ መጣች፡፡ ሊባኖስ አምስት አመት ብትቆይም ስትመለስ ምንም ብር አልነበራትም፡፡ ገንዘብ እንዲያስቀምጡ የምትልክላቸው ሰዎች ብሯን እንደካዷት ትገልፃለች፡፡ በተመለሰችበት ወቅት ዲፕሎማት ቤት ስራ አግኝታ ገባች፡፡ ለሦሥት ዓመት ከስድስት ወር ከሰራች በኋላ አሰሪዋ ቆይታዋን ጨርሳ ወደ ሀገሯ በመመለሷ እሷ ከተመለሰች በኋላ የስራ እድል የማግኘት እንዳልቻለች ትናገራለች፡፡

በ2002 ዓ.ም ልጇ 10ኛ ክፍል ማትሪክ ሲፈተን የመማር ፍላጎቱ ስለነበራት ውጤቷንም ለማሻሻል አብራው ተፈተነች፡፡ “እኔ የሙያና የቴክኒክ ውጤት ሳመጣ እሱ ፕሪፓራቶሪ የሚያስገባው ውጤት አገኘ፡፡“ ይህን ስትናገር ፊቷ ያበራ ነበር፡፡ እሱን በትምህርቱ ለማስቀጠል የአንድ አመት ከሰባት ወር ሴት ልጇን ትታ ዳግም ተሰደደች፡፡

በ2004 ዓ.ም መጀመሪ ትሰራበት ወደ ነበረ ቤት በአሰሪዎቿ ጥሪ ተጓዘች፡፡ ከአሠሪዋ ጋር መስማማት አልቻለችም፡፡ አሠሪዋ ”እኔ ነኝ ያመጣሁሽ እንደፈለኩ አደርግሻለሁ“ ትላታለች፡፡ አብራት የምትሰራው የፍሊፒን ዜጋ በህገወጥ መንገድ መምጣቷን ብትነግራትም ጣይቱ በኤርፖርት ፓስፖርት ይዛ በመውጣቷ ህጋዊ እንደሆነች ነበር የምታስበው፡፡ በአንድ አጋጣሚ ግን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሊባኖስ መግባቷን አወቀች፡፡ አጋጣሚው ይህ ነበር በሊባኖን በተፈጠረ የኢኮኖሚ ውድቀት አሠሪዎች ለሠራተኞች የሚከፍሉት በማጣታቸው መደበኛ ባልሆነ መንገድ የገቡ ሰራተኞቻቸውን ከቤት በማውጣት በየቦታው ይጥሉ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት የሚጠጡትና የሚበሉት በማጣት በከፍተኛ ችግር ውስጥ የነበሩ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግላቸው በየሶሻል ሚዲያው ድምፃቸውን ማሰማት ጀመሩ፡፡ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ዜጎቿ ወደ ሊባኖስ ጉዞ እንዳያደርጉ ማገዷን ማህበራዊ ሚዲያ ድምፃቸውን ሲሰሙ ከነበሩት ሰማች፡፡ እሷም ከእገዳው በኋላ በህገ ወጥ መምጣቷን ተገነዘበች፡፡ አሠሪዋ መደበኛ ባልሆነ መንገድ እንደወሰደቻት በማወቋ ስትዝትባት እንደነበርም ተረዳች፡፡ ከአሠሪዋ ጋር ከ6 ወር ቆይታ በኋላ በመውጣቷ ህገ ወጥ ከመሆን ባለፈም የሀገሪቱን ህግ በመጣስ ሌላ ጥፋት ማጥፋቷን ትናገራለች፡፡

በሁለተኛ ዙር ጉዞዋ ለስምንት አመታት ህገወጥ ሆና መቆየቷን የምትናገረው ጣይቱ ”ህጋዊ በሚመስል መንገድ መደበኛ ባልሆነ መንገድ መጓዜ ለብዙ መከራ እና እንግልት ዳርጎኛል“ ትላለች፡፡ ተሰባስበው ቤት ተከራይተው በሚኖሩበት በዚህ ወቅት ህገወጥ በመሆናቸው ሥራ ሰርተው ደሞዝ እንደማያገኙ፣ ሥራ ለመግባት ሄደው ተደብድበው እንደሚመለሱ እንደሚደፈሩ እንዲሁም ለረዥም ጊዜ ስራ ከሰሩ በኋላ ምንም አይነት ክፍያ ሳያገኙ ትኬት ቆርጠው እንደሚልኩ ትናገራለች፡፡ መደበኛ ባልሆነ መንገድ በመሰደዳቸው ገንዘብ የሚልኩት ህጉን ባልተከተለ መንገድ በመሆኑ ለህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር መጋለጥና የተላኩ ሰዎች ገንዘባቸውን የሚክዱበት ሁኔታም ያጋጥማቸው ነበር፡፡

በዚህ ችግር ውስጥ እያሉ የትኬት እና የሀገሪቱ መንገስት መደበኛ ባልሆነ መንገድ ወደ ሀገሪቱ የገቡ ዜጎች ላይ ያስተላለፈውን ቅጣት ከፍለው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ባቀረበው እድል ለመጠቀም በ2008 ዓ.ም ከተመዘገቡ ዜጎች ጣይቱ አንዷ ነበረች፡፡ በሀገሪቱ በነበረው የኢኮኖሚ ውድቀት በስራ እጦት ምክንያት በነበረ ችግር ለርሀብ በመጋለጧ በሽታ ላይ መውደቋን ትናገራለች፡፡ በዚህ ምክንያት ያላትን ገንዘብ ለምግብ፣ ለህክምና ለቤት ክራይ በማዋሏ ትኬቷን ችላ መመለስ ሳትችል ቀረች፡፡

በወቅቱ ኢትዮጵያ ያላቸውን ቤትና ንብረት ባለቤቷ መሸጡን በመስማቷ ይበልጥ ለጭንቀት መዳረጓን የምትናገረው ጣይቱ ”አረብ አስርቦኛል በአደራ ያስቀመጥትን ገንዘብ ግን አውድሞ የጠበቀኝ የቅርቤ ሰው ነው“ ትላለች ለዚህም ”እህቶቼ ሰርተው ገንዘባቸውን የሚያስቀምጡበት የራሳቸው የባንክ አካውንት ሊኖራቸው ይገባል“ ትላለች፡፡ ”አገር እንጂ ቤትና የሚያስብልኝ ወገን የለኝም“ በሚል ስሜት ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንደገባች ትናገራለች፡፡ ይህም ቢሆን ወደ ሀገር ቤት ተመልሳ ልጆቿን የማየት ጉጉት ተስፋዋ እንዲያንሰራራ ያደርገው ነበር፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለች ነበር የኢትዮጵያ መንግስት መደበኛ ባልሆነ መንገድ በመግባታቸው የሚከፍሉትን ቅጣት እንዲቀር ስምምነት ላይ በመድረሱ፤ የትኬት ብቻ ችለው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በ2012 ዓ.ም የተመዘገቡት፡፡ የመውጫ ቪዛ ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ በመሆኑ ቶሎ ሊመለሱ እንዳልቻሉ የምትናገረው ጣይቱ የኢትዮጵያ መንግስት ባደረገው ጥረት 2013 ዓ.ም ታህሳስ 1 ቀን ወደ ኢትዮጵያ ገብታለች፡፡ በአረብ ሀገር የ13 ዓመት ቆይታዋ ባዶ እጇን መመለሱዋል የምትገል

Mariam, [26.05.21 11:33]
ፀው ጣይቱ ልጇን አስተምራ ለቁምነገር የማድረስ ህልሟ መሳካቱን ስትናገር ፊቷ እያበራ ነው፡፡ ልጇ ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በፋርማሲ የትምህርት ክፍል በማዕረግ መመረቁን ስትናገር ጣይቱ ጀግንነት በሚነበብበት የደስታ ስሜት ተውጣ ነው፡፡

ከዛ ሁሉ መከራ በኋላ ወደ ሀገር ቤት የመጣችበትን ሁኔታ ስትገልፅ አይኖቿ በዕንባ እየረጠቡ ”እኛ በህይወት መመለስ ችለናል የሞቱ ብዙ አሉ“ የምትለው ጣይቱ በወቅቱ በህይወት ለመምጣት የትኬት 300 ዶላር የሚያስፈልግ ሲሆን የሞቱትን ለማምጣት ከ3ሺህ በላይ ዶላር ያስፈልግ ነበር ትላለች፡፡ በወቅቱ በነበረባት ችግር ትኬት መግዛት የማትችልበት ሁኔታ ውስጥ በመሆኗ ፍሪደም ፈንድ በተባለ ድርጅት ድጋፍ የትኬት ተሸፍኖላት ወደ ሀገሯ ከተመለሰች በኋላ አጋር ኢትዮጵያ ወደተባለ ድርጅት መጠለያ መግባት ችላለች፡፡ አጋር ኢትዮጵያ ከስደት ተመላሾችን በመቀበል የህክምና፣ የምግብና የመጠለያ አገልግሎት የሰጣቸው ሲሆን በመጠለያው ቆይታቸው መረጋጋት ከቻሉ በኋላ በአሁኑ ሰዓት ከጓደኞቿ ጋር በፀጉር ስራ በመሰልጠን ላይ እንደምትገኝ ትናገራለች፡፡

መንግስት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተመላሽ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እያደረጉ ያሉትን ድጋፍ ቀደም ሲል በተመለስች ሰዓት ድጋፉን ብታገኝ ኖሮ ለዳግም ስደት ላትዳረግ እንደምትችል የምታስበው ጣይቱ ከስደት ተመላሾች ከነበሩበት ሀገር ይዘው በሚመጡት የስራ እውቀት አደራጅቶ ስራ ማገናኘት ላይ ትኩረት መስጠት ይገባል ትላለች፡፡ ተመላሾች በጽዳት፣ በምግብ ሥራና በተለያዩ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው በመቆየታቸው ተደራጅተው ይህን አገልግሎት ለሚፈልግ ተቋም የሚሰሩበት ሁኔታ ቢመቻች ጥሩ መሆኑን ትጠቁማለች፡፡

ዝቅ ብሎ መስራትን እንደ ነውር ከማየት ወጥተን፤ በሀገር ውስጥ ያሉ የስራ እድሎችን በመጠቀም ከማህበራሰባችን ጋር እየኖርን በነፃነት ለመስራት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ የምትመክረው ጣይቱ ወደ ውጭ ሄደው መስራት ለሚፈልጉ ቤተሰብ ሀብትና ንብረቱን ሽጦ ልጁን ለህገ-ወጥ ደላላ ከመስጠቱ በፊት ለምን ብሎ መጠየቅ እና ክህገ-ወጥ ደላላ እራስን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ነው የምትጠቁመው፡፡ ወደ ውጭ ለሥራ በሚሄዱበት ጊዜም መስፈርቱን በአግባቡ አሟልተው ህጋዊውን መንገድ ተከትለው ሊሄዱ እንደሚገባም ትመክራለች፡፡